top of page
3priests-2048x607.jpg
የዘወትር ሰንበት ቤተክርስቲያኑ ከሌሊቱ 4 am ለምእመናን ክፍት ቢሆንም ቅዳሴ ከጧቱ 6am ጀምሮ እስከ 9:30am ይጠናቀቃል፡፡ ዘወትር ከቅዳሴ በኋላ መዝሙር በህጻናትና ወጣቶች ከቀረበ በኋላ የእለቱ ትምህርት ይቀርባል፡፡ ዘወትር እሁድ ከቅዳሴ በኋላ ከ 10 am – 11am በእንግሊዘኛ የህጻናትና ወጣቶች የተከታታይ ትምህርት ይሰጣል፡፡ በአጥብያችን ሁለት የንግስ በአላት አሉን፡፡ አንደኛው በመስከረም አሥር የሚከበረው የጼዴንያ ቅድስት ድንግል ማርያም አመታዊ በአል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መጋቢት 27 የሚከበረው የመድሐኔዓለም አመታዊ በአል ናቸው፡፡ ከሀገሩ አኗኗር የተነሳ ብዛት ያላቸው ምእመናን እንዲገኙ በማሰብ በአላቶቹ የሚከበሩት እንደ አመቺነቱ ቅዳሜ ወይም እሁድ ይሆናል፡፡ በአላቶቹ ዋዜማውን በልዩ ልዩ የስብከተ ወንጌል መርሀግብር ስናከብር ሌሊት 1am ጀምሮ በማህሌት ይከበራል፡፡​ የሰሙነ ሕማማት ዓመታዊ አገልግሎት እንደተጠበቀ ሁኖ ዘወትር የስቅለት በአል በሚከበርበት ዓርብ ከጧቱ 6am – 6pm አገልግሎት ይሰጣል፡፡​ የዳመራ በዓል ዓመታዊ አገልግሎት መስከረም ፲፮ ቀን በዋለ በሚቀርበው እሁድ ከቀኑ ፱ ሰዓት እስከ ምሽቱ ፲፪ ሰዓት Trout Lake በሚባለው ስፍራ ከሌሎች አጥብያ ጋር በጋራ ይከበራል​ ከዚህ በተጨማሪ የስብከተ ወንጌልና ልዩ ልዩ አገልግሎቶች እንደየአመቺነቱ ይካሄዳሉ፡፡

ከእናንተ አህያው ወይስ በሬው በጕድጓድ ቢወድቅ በሰንበት ወዲያው የማያወጣው ማን ነው?

1 በሰንበትም ከፈሪሳውያን አለቆች ወደ አንዱ ቤት እንጀራ ሊበላ በገባ ጊዜ እነርሱ ይጠባበቁት ነበር። 2 እነሆም፥ ሆዱ የተነፋ ሰው በፊቱ ነበረ። 3 ኢየሱስም መልሶ። በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም? ብሎ ለሕግ አዋቂዎችና ለፈሪሳውያን ተናገረ። 4 እነርሱ ግን ዝም አሉ። ይዞም ፈወሰውና አሰናበተው። 5 ከእናንተ አህያው ወይስ በሬው በጕድጓድ ቢወድቅ በሰንበት ወዲያው የማያወጣው ማን ነው? አላቸው። 6 ስለዚህ ነገርም ሊመልሱለት አልተቻላቸውም። 7 የታደሙትንም የከበሬታ ስፍራ እንደ መረጡ ተመልክቶ ምሳሌ ነገራቸው እንዲህ ሲል። 8 ማንም ለሰርግ ቢጠራህ በከበሬታ ስፍራ አትቀመጥ፤ ምናልባት ከአንተ ይልቅ የከበረ ተጠርቶ ይሆናልና አንተን እርሱንም የጠራ መጥቶ። 9 ለዚህ ስፍራ ተውለት ይልሃል፥ በዚያን ጊዜም እያፈርህ በዝቅተኛው ስፍራ ልትሆን ትጀምራለህ። 10 ነገር ግን በተጠራህ ጊዜ፥ የጠራህ መጥቶ። ወዳጄ ሆይ፥ ወደ ላይ ውጣ እንዲልህ፥ ሄደህ በዝቅተኛው ስፍራ ተቀመጥ፤ ያን ጊዜም ከአንተ ጋር በተቀመጡት ሁሉ ፊት ክብር ይሆንልሃል። 11 ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል። 12 የጠራውንም ደግሞ እንዲህ አለው። ምሳ ወይም እራት ባደረግህ ጊዜ፥ እነርሱ ደግሞ በተራቸው ምናልባት እንዳይጠሩህ ብድራትም እንዳይመልሱልህ፥ ወዳጆችህንና ወንድሞችህን ዘመዶችህንም ባለ ጠጎች ጎረቤቶችህንም አትጥራ። 13 ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ፤ 14 የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃልና። 15 ከተቀመጡትም አንዱ ይህን ሰምቶ። በእግዚአብሔር መንግሥት እንጀራ የሚበላ ብፁዕ ነው አለው። 16 እርሱ ግን እንዲህ አለው። አንድ ሰው ታላቅ እራት አድርጎ ብዙዎችን ጠራ፤ 17 በእራትም ሰዓት የታደሙትን። አሁን ተዘጋጅቶአልና ኑ እንዲላቸው ባሪያውን ላከ። 18 ሁላቸውም በአንድነት ያመካኙ ጀመር። የፊተኛው። መሬት ገዝቼአለሁ ወጥቼም ላየው በግድ ያስፈልገኛል፤ ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ አለው። 19 ሌላውም። አምስት ጥምድ በሬዎች ገዝቼአለሁ ልፈትናቸውም እሄዳለሁ፤ ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ አለው። 20 ሌላውም። ሚስት አግብቼአለሁ ስለዚህም ልመጣ አልችልም አለው። 21 ባሪያውም ደርሶ ይህን ለጌታው ነገረው። በዚያን ጊዜ ባለቤቱ ተቆጥቶ ባሪያውን። ወደ ከተማ ጎዳናና ወደ ስላች ፈጥነህ ውጣ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንና ዕውሮችንም ወደዚህ አግባ አለው። 22 ባሪያውም። ጌታ ሆይ፥ እንዳዘዝኸኝ ተደርጎአል፥ ገናም ስፍራ አለ አለው። 23 ጌታውም ባሪያውን። ቤቴ እንዲሞላ ወደ መንገድና ወደ ቅጥር ውጣና ይገቡ ዘንድ ግድ በላቸው፤ 24 እላችኋለሁና፥ ከታደሙት ከእነዚያ ሰዎች አንድ ስንኳ እራቴን አይቀምስም አለው። 25 ብዙም ሕዝብ ከእርሱ ጋር ይሄዱ ነበር፥ ዘወር ብሎም እንዲህ አላቸው። 26 ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። 27 ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። 28 ከእናንተ ግንብ ሊሠራ የሚወድ ለመደምደሚያ የሚበቃ ያለው እንደ ሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ ከሳራውን የማይቈጥር ማን ነው? 29 ያለዚያ መሠረቱን ቢመሠርት፥ ሊደመድመውም ቢያቅተው፥ ያዩት ሁሉ። 30 ይህ ሰው ሊሠራ ጀምሮ ሊደመድመው አቃተው ብለው ሊዘብቱበት ይጀምራሉ። 31 ወይም ሌላውን ንጉሥ በጦርነት ሊጋጠም የሚሄድ፥ ከሁለት እልፍ ጋር የሚመጣበትን በአንድ እልፍ ሊገናኝ የሚችል እንደ ሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ የማያስብ ንጉሥ ማን ነው? 32 ባይሆንስ ሌላው ገና ሩቅ ሳለ መልክተኞች ልኮ ዕርቅ ይለምናል። 33 እንግዲህ እንደዚሁ ማንም ከእናንተ ያለውን ሁሉ የማይተው ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። 34 ጨው መልካም ነው፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፈጣል? 35 ለምድር ቢሆን ለፍግ መቈለያም ቢሆን አይረባም፤ ወደ ውጭ ይጥሉታል። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።

የሉቃስ ወንጌል፤ ምዕራፍ 14

Sacraments & Services

Liturgical Calendar

Library

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • Instagram

የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለምና ጼዴንያ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን

Miskay Hizunan Medhanealem & Tsedenia Kidist Mariam Church

628 Royal Avenue, New Westminster, British Columbia

bottom of page